በኢትዮጵያ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከመመረጣቸዉ በፊት በነበሩት
ዓመታት በአገሪቱ የሰብአዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ ሲወጡ በነበሩ መረጃዎች ላይ በመንተራስ በአሜሪካን መንግስት ሁለቱም ምክር ቤቶች/ባለፈዉ በኮንግረሱ አሁን ደግሞ በሴኔቱ ድጋፍ
አግኝቶ ባለፈዉ ሳምንት የጸደቀ የመንግስት አቋም/ H.Res.128
- Supporting
respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia/ በኢትዮጵያ የሰብአዊ
መብት መከበር እና ሁሉን የፖለቲካ ዓካላት አሳታፊ የሆነ መንግስት እንዲቋቋም መርዳት/ የሚል ነዉ ዓላማዉ፡፡
ዋና ዋና ነጥቦቸም፡-
- የአስቸኳይ
ግዜ አዋጁን መነሳት ጨምሮ የጸጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ ኃይለል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እንዳይወሰድ እና
- እስካሁን
በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የደረሰዉ የሞት ከመጠን ያለፈ ኃይል ጥቅም ላይ ስለመዋሉ የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት
ጥሰትን የሚመረምር መርማሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ፤
- እንዲሁም እንዲሻሩ የተጠየቁ የኢፌድሪ ህጎች ፡- ሰላማዊ የፖለቲካ
ተቃዉሞ እና የመናገር የመጻፍ ነጣነትን የሚገድቡ ህጎች፤ ከመሬታቸዉ የተፈናቀሉ ባለይዞታዎች በፍርድ ቤት መብታቸዉን
እንዳይጠይቁ የሚከለክል ህግ፤ ሰላማዊ ሰልፈኞችን እና ሰላማዊ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን የመሰብሰብ እና ሃሳባቸዉን
በነጻነት ለመግለጽ እንዳይችሉ ህጋዊ መብታቸዉን በመገደብ እንዲታሰሩ የሚፈቅድ ህግ እና ሰላማዊ የበጎ አድራጎት
እንቅስቃሴን ለመገደብ የወጡ ህጎች እንዲሻሩ፡፡.
- ከዚህ
የተነሳም በኢትዮያ ዉስጥ የተፈጠረዉ ሰብአዊ እና ፖለቲካዊ ቀዉስ ይሻሻል ዘንድ የሚመለከተዉ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር
በኩል ለጉዳዩ አጽንኦት ሰጥቶ በኢትዮጵያ የመልካም አሰተዳደርና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ድጋፍ እንደሚያደርግ እና ከአሜሪካ
የገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በዉጪ አገር በሚፈጸሙ ከህግ ዉጪ በሚወሰድ የግድያ ፤አካላዊ ስቃይ/ቶርቸር/ እና
ሌሎች በአለም አቀፍ ደረጃ የተወገዙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ በተሳተፉ ግለሰቦች ላይ ሊወሰድ የሚገባዉ እነርምጃ በኢትዮጵያ
ዉስጥ ለተፈጸመዉ አስፈላጊዉን ህጋዊ ማእቀብ እንዲያደርግ የሚጠይቅ ነዉ፡፡
የቀድሞ
ኢሀዴግ ባለስልጣናት ለምን ተቃወሙት ?
ለዚህ ሁለት ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
አንደኛዉ- ይህ የአሜሪካ አቋም ከሀገሯ ዉጪ ባለ ሌላ አገር ላይ መቅረቡ ሉአላዊነትን የሚጥስ በመሆኑ ነዉ ሊያስብል ይችላል፡፡
በሁለተኛነት ደግሞ - ከሉአላዊነት ጥያቄ በመለስ በባለስልጣናቱ ህልዉና ላይ የሚመጣዉ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ተጽእኖ የበለጠ ስጋት
በመሆኑ ነዉ ሊባልም ይችላል፡፡
የ H.Res.128 - እንዴት ተፈጻሚይሆናል ?
ከላይ የተጠቀሱት የአሜሪካ መንግስት የአቋም ነጥቦች በተግባራዊነታቸዉ ላይ እንቅፋት
ቢፈጠር በአቋም መግለጫዉ የመጨረሻ ነጥብ ላይ የተጠቀሱት አካላት ማለትም የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ማስሪያ
ቤት ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ነዉ፡፡ ግን እንዴትና በምን አለማቀፋዊ ህግ እንደሚጠቀሙ መግለጹ አስፈላጊ ነዉ፡፡ በኦባማ
ፕሬዘዳንትነት ዘመን በ2012 እ.ኤ.አ ማለት ነዉ በራስያ ዉስጥ ማግኔትሰኪ ሚባል የሂሳብ ባለሙያ/አካዉንታንት/ የተፈጸመ
ከፍተኛ የባለሃብቶች የታክስ ማጭበርበርን በማጋለጡ ምክንያት ከባለሃብቶች ዉስጥ ከፍተኛ የሩስያ ባለስልጣናት ስለ ሚገኙበት
እነሱ ማግኔትስኪ እንዲታሰር አድርገዉ በታሰረበት ደግሞ በተፈጸመበት ከፍተኛ የአካል ስቃይ/ቶርች/ እዚያዉ እስር ቤት ዉስጥ
ህይዎቱ አልፏል፡፡ በዚህ መነሻነት አሜሪካ በዉጭ ጉዳይ ግንኙነቷ በዚህ ሰዉ ላይ ለደረሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተዋናይ
በሆኑት የሩስያ ባለስልጣናት ላይ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የቪዛ ክልከላ እንዲሁም በአሜሪካና የአሜሪካ አጋር በሆኑ አገሮች
ያላቸዉን የባንክ አካዉንት እንዲታገድ በማድረግ እርምጃ ለመዉሰድ የሚያስችል በሩስያ ላይ ብቻ ያተኮረ የ Magnitsky Act የሚባል ህግ አዉጥታ ተግብራዋለች፡፡
የአሜሪካ
አለማቀፍ ማግኒትስኪ ህግ(The US
Global Magnitsky Human Right Accountability Act)
ያሁኑ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከያዙ በኋላ ደግሞ ይህንኑ ህግ በአለም
አቀፍ ደረጃ ከሌሎች አገሮች ጋር ባላት ግንኙነት ለመጠቀም በማሰብ
በ2016 እ.ኤ.አ The US Global
Magnitsky Human Right Accountability Act ብላ በመሰየም በፕሬዚዳንቱ አቅራቢነት የአሜሪካ ምክር ቤት ጸድቋል፡፡ ይህም ህግ ለፕሬዚዳንቱ የሚከተሉትን
ስልጣን ይሰጣል፡፡
ሀ- ከህግ ዉጪ በተፈጸመ ግድያ፤ቶርቸር እና ሌላ በአለም አቀፍ ደረጃ ከባድ ወንጀል በሆነ
ድርጊት ላይ በመብት ጥስት ተጠያቂ ለሆነ አካል ተወካይ በመሆን የተሳተፉ፤ እና
ለ- እንዲሁም በከፍተኛ
የሙስና ተግባር ዉስጥ የተዘፈቁ የመንግስት ባለስልጣናት ወይም የባለስልጣናቱ ከፍተኛ ተባባሪ የሆኑ ግለሰቦችን በመብት ጥሰት ላይ የተሳተፉ የዉጭ
አገር ዜጎች/ባለስልጣናት እና ተቋሞች ላይ ወደ አሜሪካ መግቢያ ቪዛ መከልከል ወይም መንጠቅ ወይም በሃብታቸዉ ላይ እገዳ
ማስደረግ እንደሚችል ነዉ፡፡
ምን ህጋዊ ተጽእኖ ሊኖረዉ ይችላል?
-
ይህ የማግኔትስኪ ህግ በባህሪዉ
የፍትሃብሄር ህግ እንጂ የወንጀል ህግ አይደለም፡፡ ስለሆነም
የአሜሪካ ፐርዚዳንት ጽ/ቤት በዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና በገንዘብ
ምኒስትሩ አማካይነት ከዚህ በላይ በ ሀ እና ለ ስር በተጠቀሱ ድርጊቶች ላይ ለመሳተፋቸዉ በቂ ማስረጃ በሚቀርብባቸዉ ላይ የአሜሪካ መግብያ ቪዛ
ክልከላና ቀድሞዉን ያላቸዉ ከሆምነ የመነጠቅ እድል የሚገጥማቸዉ ሲሆን በተጨማሪም በአሜሪካ እና የአሜሪካ አጋር በሆኑ አገሮች
ባንኮች ዉስጥ በራሳቸዉ ስም ፤ቤተሰብ ወይም የቅርብ ዘመድ ስም በተከፈተ አካዉንት ያላቸዉ ገንዘብ በተመለከተ አስቀማጩ ባንኩ
ሊጠብቅላቸዉ የሚገባዉን ያለባለገንዘቡ ፍቃድ ለሶስተኛ ወገን መስጢር ያለመስጠት መብታቸዉ ተሰርዞ መረጃዉ እንዲጋለጥ ማስደረግ
እና ከዚህ ከፍ ሲልም ገንዘቡ እንዳይንቀሳቀስ እገዳ ሊጣልበት ይችላል፡፡
-
ከዚህ ሌላ ደግሞ በተለይ በ ሀ ስር የተዘረዘሩትን
ድርጊቶች መፈጸም ሌላ የሚያስከትለዉ ህጋዊ እርምጃ አለ፡፡ ድርጊቶች በባህሪያቸዉ በሰዉ ልጆች ሰብአዊ ክብር/Human
dignity/ላይ የሚፈጸሙ ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ተብለዉ እዉቅና የተሰጣቸዉ ሲሆኑ በተለይም ከፍተኛ የአካልና እና ህሊና
ስቃይ የሚያደርሱ ቅጣቶች/Torture/ በአለም አቀፍ ህግ ዉስጥ በሰዉ ልጅ ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች እንደ ዘር ማትፋት ወንጀል
ሁሉ የመጨረሻ ከባድና አረመኔያዊ ወንጀሎች ተብለዉ ተለይተዉ ከሚታወቁት አንዱ ነዉ ፡፡ ከዚህም የተነሳ ምንም እንኳ ሌሎቹ
የወንጀል ህግ ጥሰቶች ድርጊቶቹ በተፈጸሙበት አገር ዉስጥ ባሉት ፍ/ቤቶች ብቻ ተወስነዉ የሚታዩ ቢሆነም በነዚህ ወንጀሎች
አፈጻጸም ተካፋይ የሆነ ተጠርጣሪ ግለሰብ ግን በአለም አቀፉ የወነጅል ፍ/ቤት ወይም ወንጀሉን ፈጽሞ ወደ ሌላ አገር እንኳ
ተሰዶ መኖሪያዉን እዚያዉ ቢያደርግ እሱ የሚኖርበት ማንኛዉም አገር ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት እዚያዉ ሊዳኝ ይችላል፡፡ ለዚህ
ጥሩ ምሳሌ የሚሆነዉ በደርግ መንግስት በዚህ ዓይነት ድርጊት ተሳትፈዉ ነበር የተባሉ ኢትዮጲያዉያን ተሰደዉ ሲኖሩበት በነበረዉ
አሜሪካ እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ በኔዘርላንድ ተይዘዉ ለፍርድ በመቅረብ የፍርድ ቅጣት ያገኙበት ታሪክ አለ፡፡
-
ከዚህ አንጻር በተጠቀሱት የህገወጥ ግድያ እና ቶርተር ወንጀሎች ላይ
ስለመሳተፋቸዉ የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ አሜሪካ የአለማቀፍ ማግኔትስኪ ህጓን ለማስፈጸም በባለስልጣናቱ ላይ በምታደርገዉ
ምርመራ/investigation/ ዉጤት በአለም አቀፍ ፍ/ቤት ወይም እዚሁ በኢትዮጵያ ፍ/ቤት ክስ የሚቀርብባቸዉ ከሆነ
በማስረጃነት ሊቀርብባቸዉ የሚችል በመሆኑ ሃብታቸዉን መዉረስ ጨምሮ ተጽእኖዉ ከባድ ነዉ የሚሆነዉ፡፡በቀድሞዉ የኮትዲቯር
ፕሬሲዳንት ሎራን ባግቦ ላይ እንደሆነዉ ዓይነት ዉጤት ሊያስከትልባቸዉ ይችላል ፡፡
-
ስለሆነም ምናልባት በደቡብ አፍሪካ
አፓርታይድ ዘመን በጥቁሮች ላይ ባለስልጣነቱ ሲፈጸሙና ሲያስፈጽሙት የነበሩዉ ከባድ ከባድ አለማቀፋዊ ወንጀሎች የሰላማዊ
የፖለቲካ ስልጣን ሽግግርን ለትግሉ ዋና ምላሽ በመዉሰድ በአለማቀፉ ማህበረሰብ ግፊት ጭምር በማንዴላ “ብቀላን በፍቅር- ይቅር
እንባባል” ዉሳኔ ዓይነት በኢትዮጵያ መንግስት እንዲያዉ ለምናልባት ካልታለፉ በቀር ፡፡https://www.facebook.com/settings?tab=account§ion=usernamehttps://goo.gl/maps/VEZdbNBb36v
Melaku, Though I don't under what Law is in African Context, It is very creative art to have this blog and teach the Ethiopian community for safety, security and Rule of Law. Continue writing every day on this subject and other Law issues that our people in dire needy.
ReplyDeleteIt would be very dangerous for the corrupted powers if any, but do these corrupted people have an exit plan? If a man really uses his head, why never sense a bit to feel certain on the consequences of that action. ALAS??>
ReplyDelete