በአሜሪካዉ ሴኔት የጸደቀዉ (H.Res.128) እና የሚያሳድረዉ ተጽእኖ
በኢትዮጵያ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከመመረጣቸዉ በፊት በነበሩት ዓመታት በአገሪቱ የሰብአዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ ሲወጡ በነበሩ መረጃዎች ላይ በመንተራስ በአሜሪካን መንግስት ሁለቱም ምክር ቤቶች/ባለፈዉ በኮንግረሱ አሁን ደግሞ በሴኔቱ ድጋፍ አግኝቶ ባለፈዉ ሳምንት የጸደቀ የመንግስት አቋም/ H.Res.128 - Supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia/ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት መከበር እና ሁሉን የፖለቲካ ዓካላት አሳታፊ የሆነ መንግስት እንዲቋቋም መርዳት/ የሚል ነዉ ዓላማዉ፡፡ ዋና ዋና ነጥቦቸም፡- የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን መነሳት ጨምሮ የጸጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ ኃይለል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እንዳይወሰድ እና እስካሁን በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የደረሰዉ የሞት ከመጠን ያለፈ ኃይል ጥቅም ላይ ስለመዋሉ የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ጥሰትን የሚመረምር መርማሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ፤ እንዲሁም እንዲሻሩ የተጠየቁ የኢፌድሪ ህጎች ፡- ሰላማዊ የፖለቲካ ተቃዉሞ እና የመናገር የመጻፍ ነጣነትን የሚገድቡ ህጎች፤ ከመሬታቸዉ የተፈናቀሉ ባለይዞታዎች በፍርድ ቤት መብታቸዉን እንዳይጠይቁ የሚከለክል ህግ፤ ሰላማዊ ሰልፈኞችን እና ሰላማዊ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን የመሰብሰብ እና ሃሳባቸዉን በነጻነት ለመግለጽ እንዳይችሉ ህጋዊ መብታቸዉን በመገደብ እንዲታሰሩ የሚፈቅድ ህግ እና ሰላማዊ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴን ለመገደብ የወጡ ህጎች እንዲሻሩ፡፡. ከዚህ የተነሳም በኢትዮያ ዉስጥ የተፈጠረዉ ሰብአዊ እና ፖለቲካዊ ቀዉስ ይሻሻል ዘንድ የሚመለከተዉ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር ...